Back to Search

?? ???: Historical Novel

AUTHOR Degiffe, Abera Lemma
PUBLISHER Abera Lemma (09/23/2022)
PRODUCT TYPE Paperback (Paperback)

Description
ይህ የሥነ-ጽሁፍ ሥራ በታሪካዊ ልቦለድነቱ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ወግም አስፈላጊው ትኩረት እንዳይነፈገው ጥረት ተደርጓል፡፡ የተወሰነ ዘመንን ተንተርሷል፤ ከደርግ አሥራ ሰባት ያገዛዝ ዘመን... አሥራ አራቱን፡፡ የዘመነ ደርግን ምሥጢራዊ ሰነዶችና መዛግብቶችን፤ ከተነሳበት ጭብጥ አኳያ ፈትሿል፡፡ በዚህም ጠቃሚ መረጃዎችን ለታሪካዊነቱ ዋቢ አድርጓል፡፡ "ታሪካዊ ልቦለድ በኃላፊ ጊዜ ቢጋር ውስጥ ተቀንብቦ ከባለታሪኮቹና ከመረጃዎች ጋር ቁርኝት ቢኖረውም፤ የዘመኑን ትንሣኤና ውድቀት አበክሮ ከማውሳት አያልፍም'' የሚለውን የብዕሩን ሰው የአንቶኒ ትሮሎኘን ነቢብ መደላድሉ አድርጓል፡፡ ከእንግሊዛዊው የታሪካዊ ልቦለድ ደራሲና ገጣሚ ከሮበርት ግሬቭ የግል አስተያየት ጋርም ደራሲው የሚስማማበት ነጥብ አለው፡፡ ግሬቭ፤ "እራሴን ወደ ቀድሞ ዘመንና ትዝታዎች የመመለስ ስጦታው አለኝ፡፡ በዚህም ትናንት ምንና እንዴት እንደነበር ማየት እችላለሁ፡፡ ታሪካዊ ልቦለድም መጻፍ ያለበት በዚህ መልክ ነው፡፡'' ይላል፡፡

ይህ ታሪካዊ ልቦለድ ባንድ የደርግ ቋሚ ኮሚቴ አባል በነበረ ግለሰብ ሕይወት ዙሪያ የተጠነጠነ ነው፡፡ የግለሰቡን መነሻና መድረሻ፣ ከደርግ ሥልጣነ ዘመን ቆይታ ጋር ይመለከታል፡፡ በአብዮቱ ዘመን ውጣ ውረድ ውስጥ ያብዮተኞች እጣ ፈንታና መጨረሻ ምን እንደነበር በመረጃዎች ተደግፎ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ጥበብ አኳያ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ ሥልጣን ያሰከራቸው ለማንም ለምንም እንደማይመለሱ ተስተውሏል፡፡ አንድ ዕውቅ ያገራችን ባለቅኔም፤

'አንቺ የሥልጣን ፅዋ፣ ሲይዙሽ በተራ

ገፈታሽ ጣፋጭ ነው፣ ጭላጭሽ መራራ፤

ይኸንን እያየ፣ የሚተውሽ የለም

ይጋደልብሻል፤ የሰው ልጅ ዘላለም፤'

ሲሉም የባለጊዜዎችንና የመንበራቸውን ፍጻሜ ያመለከቱት ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡

Show More
Product Format
Product Details
ISBN-13: 9789994437566
ISBN-10: 9994437569
Binding: Paperback or Softback (Trade Paperback (Us))
Content Language: Amharic
More Product Details
Page Count: 484
Carton Quantity: 14
Product Dimensions: 5.83 x 1.08 x 8.27 inches
Weight: 1.38 pound(s)
Country of Origin: US
Subject Information
BISAC Categories
Fiction | Historical - General
Descriptions, Reviews, Etc.
publisher marketing
ይህ የሥነ-ጽሁፍ ሥራ በታሪካዊ ልቦለድነቱ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ወግም አስፈላጊው ትኩረት እንዳይነፈገው ጥረት ተደርጓል፡፡ የተወሰነ ዘመንን ተንተርሷል፤ ከደርግ አሥራ ሰባት ያገዛዝ ዘመን... አሥራ አራቱን፡፡ የዘመነ ደርግን ምሥጢራዊ ሰነዶችና መዛግብቶችን፤ ከተነሳበት ጭብጥ አኳያ ፈትሿል፡፡ በዚህም ጠቃሚ መረጃዎችን ለታሪካዊነቱ ዋቢ አድርጓል፡፡ "ታሪካዊ ልቦለድ በኃላፊ ጊዜ ቢጋር ውስጥ ተቀንብቦ ከባለታሪኮቹና ከመረጃዎች ጋር ቁርኝት ቢኖረውም፤ የዘመኑን ትንሣኤና ውድቀት አበክሮ ከማውሳት አያልፍም'' የሚለውን የብዕሩን ሰው የአንቶኒ ትሮሎኘን ነቢብ መደላድሉ አድርጓል፡፡ ከእንግሊዛዊው የታሪካዊ ልቦለድ ደራሲና ገጣሚ ከሮበርት ግሬቭ የግል አስተያየት ጋርም ደራሲው የሚስማማበት ነጥብ አለው፡፡ ግሬቭ፤ "እራሴን ወደ ቀድሞ ዘመንና ትዝታዎች የመመለስ ስጦታው አለኝ፡፡ በዚህም ትናንት ምንና እንዴት እንደነበር ማየት እችላለሁ፡፡ ታሪካዊ ልቦለድም መጻፍ ያለበት በዚህ መልክ ነው፡፡'' ይላል፡፡

ይህ ታሪካዊ ልቦለድ ባንድ የደርግ ቋሚ ኮሚቴ አባል በነበረ ግለሰብ ሕይወት ዙሪያ የተጠነጠነ ነው፡፡ የግለሰቡን መነሻና መድረሻ፣ ከደርግ ሥልጣነ ዘመን ቆይታ ጋር ይመለከታል፡፡ በአብዮቱ ዘመን ውጣ ውረድ ውስጥ ያብዮተኞች እጣ ፈንታና መጨረሻ ምን እንደነበር በመረጃዎች ተደግፎ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ጥበብ አኳያ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ ሥልጣን ያሰከራቸው ለማንም ለምንም እንደማይመለሱ ተስተውሏል፡፡ አንድ ዕውቅ ያገራችን ባለቅኔም፤

'አንቺ የሥልጣን ፅዋ፣ ሲይዙሽ በተራ

ገፈታሽ ጣፋጭ ነው፣ ጭላጭሽ መራራ፤

ይኸንን እያየ፣ የሚተውሽ የለም

ይጋደልብሻል፤ የሰው ልጅ ዘላለም፤'

ሲሉም የባለጊዜዎችንና የመንበራቸውን ፍጻሜ ያመለከቱት ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡

Show More
List Price $20.99
Your Price  $20.78
Paperback